hawi book store

hawi book store Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from hawi book store, Book shop, abosto, Shashemene.

ዘለሰኛ ሂሶች( ሀገር ፣ ጥላና ዘመን)በደራሲ እንዳለጌታ ከበደ « ሲጥል »  መጽሐፍ ላይ የተደረገ መጠነኛ ዳሰሳበሲራክ ወንድሙ ክፍል - 1ራሺያ በጎጎል ካፖርት ውስጥ የተደበቀች ሀገር መሆኗ...
27/08/2024

ዘለሰኛ ሂሶች
( ሀገር ፣ ጥላና ዘመን)

በደራሲ እንዳለጌታ ከበደ « ሲጥል » መጽሐፍ ላይ የተደረገ መጠነኛ ዳሰሳ

በሲራክ ወንድሙ

ክፍል - 1

ራሺያ በጎጎል ካፖርት ውስጥ የተደበቀች ሀገር መሆኗን በስነ ፅሁፍ አለም መረዳት ከቻልን የአፍሪካውያንን ብሎም የኢትዮጵያን ዘለሰኛ የኑረት ማህተም የምንፈትሸው ከተሰዳጅ የእግር አሻራው መሀል ቢሆንስ?

ከሚስጥራዊ የመቃብሮቻችን አፈር ላይ የበቀለ የአፀድ ቅርንጫፍ ላይ ያረፉ ወፎች እንዴት ለእኛ የሚሆን ዜማ አጡ? ታሪካችን ሁሉ ሲሄዱ ሲሄዱ መንገድ ላይ አለቁ እንጂ መንገድ አለቀ የሚል መደምደሚያ አለው?

መግቢያ

ሀገር የህልመኞች ውጥን ናት። የሩቅ አሳቢ ተጓዦች ምጥንም ጭምር..! የሚመጣው ትውልድ የሚመጣው የሄደው ትውልድ በረገጠበት የእግር ዳናው ስፍር ነው። ታሪካችን በሰርዶ ሳር መሀል እግር እንዳበጀው ቀጭን የገጠር መንገድን ይመስላል።

ሀገር፤ ሁሉ በዘፈቀደው የብርሃኑ ጭልታ የቸገረው ምንደኛ የሚጨልጣት ፅዋ ሳትሆን ጥሙን እያስታመመ ለመጪው ትውልድ የሚቆጥባት የመቀነት ዳሩ እውነት ነች። ልቦና ካላዛለው የእምነት ሸክም የተገነባ ማህበረሰብ ቤቱን እያቃጠለ ክረምቱን ልወጣ አይልም። አብሮ መቆም የሚሰጠውን ደጀን በመነጣጠል ጦርና ጎራዴ አይበትነውምና..!

ሀሳብ እነዚህን ተሻጋሪዎች ለማሻገር የምንጠቀምበት ስሁት ድልድያችን ነው። ከሀሳብም ሀሳብ.. ከድልድይም ኪነት!

ሲጥል የአርአያችን ፤ የዘመኑ ትሁት አባት ፤ የትውልድን ሸክም ብቻውን በመወጣት የሚታትረው ሰው ረጅም ልቦለድ ነው። በስደተኛ የገፀባህሪያት ዶቃ ክሩን ውበት እያደረገ የሰፋልን ውብ ጌጥ..!

መፅሀፉን በ 280 ገፅና በ14 ምዕራፍ እንዲሁም በ 98 ንዑስ ርዕስ ከፋፍሎ አቅርቦታል።

ከጀርባው ላይም እንደተገለፀው አደራደራቸው የጃዝ ሙዚቃን ቅርፅ የተላበሱ ናቸው። ንዑስ ርዕሶቹ ስር ያሉ ተረኮች ብቻቸውን ሲሆኑ ትርጉም የሚሰጡ፣ጠረን ያላቸው፣ ነጠላ ህይወት የተቸሩ መዳረሻዎችን ያቀፉ ሲሆን በምዕራፍ ሲገመዱ ደግሞ ህብረ ዝማሬ ሆነው ቀጣዩ ጣዕምስ ምንድነው የሚያስብሉ ናቸው።

ስድሩ በአማረኛ ፊደላት ከሀ ማለዳ እስከ ቀትር ( ምሽት )ነ የፊደል ድርድር ሽሩባ ይመስል የወረደ መልካ ነው። ( ከሀ እስከ ነ ያሉት ፊደላት እንደምዕራፍ ሲያገለግሉ ምንዝር ፊደላቶቹ ( ( ከሀ - ሆ ) ) ያሉት በንዑስ ርዕስነት ያገለግላሉ። )

እርስ በርሱ የተሳሰረበት ገመድ ለአንባቢው ረፍት ነሺና ወደፊትም አንደርዳሪ ነው።

የአተራረክ ዘይቤውን በተመለከተ ወይም የቀለም ጥላውን ስያሜ ስለካ በግሌ ይሄን መፅሀፍ በሁለት እከፍለዋለሁ። ይኸውም ዐሊይ መንደር እስኪገቡ ያለው ምዕራፍ ስነ ፅሁፋዊ ስልቱ ቦታን ፤ ሁኔታን ጊዜና ዕይታን በተባ ብዕሩ ለመግለፅ የሞከረ ብሎም የተሳካለት ሲሆን ከዐሊይ መንደር ትውውቅ በኋላ ምናልባትም እስከመጨረሻው አዳዲስ ክስተታዊ ፣ ምልሰታዊ ና ሀሳባዊ የቅርርቦሽ ቁጭቶችን ያጣመረ ይመስለኛል። ልክ እንደወገብ መቀነት ቁጥር ፈታ ሸምቀቅ ደግሞም ቁጥር የሚለውን የፍሰቱን ማዕድ ከብቦ የተቀመጠ ልብ ገና ቡራኬ ፀሎቱ ወገቡ ላይ ሳይደርስ በመስገብገብ እጁን ከመስደድ አይሰንፍም።

ደቂቅ የተፈጥሮ ሁነታዊ በረከቶችን አኳኳል ቅሽር ካለው የገለፃ መደብ ስር ስደረድረው በረሃ በዋለ ገላ ቀዝቃዛ ውሃ ቸልሶ ከሙቀቱ ምጡ የመገላገል ያህል ነው።

( እንኳን ማሪያም ማረችን..!..........................

ስልክ :-0992653968
0911704376

10/08/2024
.         በዓሉ ግርማ :ኦሮማይ በነገሮች አጋጣሚ ስለ በዓሉ ግርማ ሳትሰሙ ምትቀሩ አይመስለኝም።በተለይ የዛሬን አያድርገውና   ትምህርት በነበረበት ሰዓት ስለ ነጭ ሽብር ስንማር ምሳሌ ...
25/07/2024

. በዓሉ ግርማ :ኦሮማይ
በነገሮች አጋጣሚ ስለ በዓሉ ግርማ ሳትሰሙ ምትቀሩ አይመስለኝም።በተለይ የዛሬን አያድርገውና ትምህርት በነበረበት ሰዓት ስለ ነጭ ሽብር ስንማር ምሳሌ የምናደርገው በዓሉን ነበር።ለምን?ቢሉ የት እንደገባ፣ማን እንዳፈነው፣የት እንዳደረሱት አይታወቅምና!!!
መፅሐፉ ራሱ ከሌሎች መፅሐፍ በተለየ የፊት ሽፋኑ ይለይባችኋላ።አብዛኞቹ ደራሲያ ስማቸው ከርዕሳቸው ግርጌ ላይ ለዛውም በትንሹ ነው ሚያኖሩት።
በዓሉ ግርማ ግን ኦሮማይን ከፃፈ በኋላ እንደ ሌሎቹ ግርጌን አልመረጠም።ራስጌም አላሻውም ብል ማካበድ አይሆንም።ስሙን አጉልቶ
"
በዓሉ ግርማ
ኦሮማይ"
አለ።እንግዲህ በመፅሐፉ የውስጥ ገፅ 'ኦሮማይን"ሲፈታው "አለቀ አበቃ"ብሎ ነው።አንድ ላይ ስናገጣጥመው "በዓሉ ግርማ አለቀለት፣አበቃለት"የሚል ትርጉም ይሰጠናል።
እንደሚያበቃለት፣እንደሚያልቅለት ተልሞ የፃፈው መፅሐፍ ምን አይነት መፅሐፍ ነው?ብሎ የማይጠይቅ ለኔ ጋናዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለም።

ለማበር ያህል መቼስ የበዓሉ ግርማ ሴቶች ሲባል ሳትሰሙ አትቀሩም።አንድ ጥናታዊ ፅሑፍ አለ እሱን መመልከት ትችላላችሁ።እና ከአምስቶቹ አንዷ ፌያሜት ጊላይ ነች።የአስመራዋ ኮከብ እዚያ ውስጥ ታገኟታላችሁ።አቦ ደስ ስትል እኮ!...ስንት empity set()ባለበት ሀገር እሷ ግን empity ሴት አልነበረችም።ፀጋዬ እንዲህ ይላታል።"ቆንጆ ነሽ በእውነት...ሰሜናዊት ጽብቅቲ...የቀይ ባህር ርግብ"
ሞሞላቀቅ በፊያሜታ የቀረ ይመስለኛል።በሷ አሞላቀቅ ሌሎች ሴቶች ሲሞላቀቁ ስታዩዋቸው የሆነ አንቃችሁ ግደሏቸው ግደሏቸው ነው ሚያሰኘው።

ፊያሜታ ከፀጋዬ ጋር በምታደርገው ንግግር ትረካችንን እንቋጭ።

"...እውይ ፀግዬ!ግን ምን አይነት ሴት ነኝ?እስቲ ንገረኝ"አለች
"ጣፋጭ"አልኳት!
"ደደብ ነህ አባቴ ይሙት..."
"አንቺ ልጅ ተይ ደደብ አትበይኝ"አልኳት
"ለምን እስቲ ንገረኝ"አለች
"በሀገራችን ወንድ ይከበራል፤መከበር አለብኝ"
"እውይ ማን አለህ?"
"አውቃለሁ።ገዝሚ የማትሰጥ ሴት ባል አታገኝም።እና ታዲያ ይህ ማለት ምን ይመስልሻል?ወንድ ክቡር ነው ማለት ነው።አይደለም?"
"ደደብ።አባቴ ይሙት ደደብ ነህ።ለምንድነው ግን ደደብ የምልህ?ምን አይነት ሴት ነኝ!?
"ጣፋጭ"አልኳት ይለናል።

እንደማትመር ምስክር ነኝ።ደስስስስስስ ስትል የምር!!!...የሆነ በአካል የምታቋት ያህል ታጫውታለች።

ማሳሰቢያ፦
መፅሐፉ እስከ ገፅ 130 ድረስ እጅግ አሰልቺ በመሆኑ እንዳተውት።ለምን ይህን ያህል ቆመጠጠ?ያን ሁሉ ገፅ'ብዬ ጠይቄ ነበር።ለካ ፊያሜታ ምትገባው ከዚያ በኋላ ነው።

መልካም ንባብ!!
#ኦሮማይ..........................

ስልክ :-0992653968
0911704376

ሐዲስ(በዓሉ ግርማ )"በዓሉ ግርማ የአማርኛ ስነ ጽሁፍ በቄብነት ዘመኗ ካፈራቻቸው የበህር ደራሲዎች መካከል አንዱ ነው "                                  #አሌክስ ከበዓሉ...
24/07/2024

ሐዲስ(በዓሉ ግርማ )

"በዓሉ ግርማ የአማርኛ ስነ ጽሁፍ በቄብነት ዘመኗ ካፈራቻቸው የበህር ደራሲዎች መካከል አንዱ ነው "
#አሌክስ
ከበዓሉ ግርማ ስራዎች አንዱ የሆነው
#ሀዲስ እጅግ የተወደደ እና አሪፍ መጽሐፍ ነው። መጻሐፉ በገጸ ባህርይ አሳሳል በመቼት መረጣ እንዲሁም በትልሙ የተዋበ ነው ።የመጸሐፉ ይዘት ሙሉ በሙሉ ማለት በምንችልበት ደረጃ የተማሪዋቹ እንቅስቃሴ የ66ቱ አብዮት እና የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አወዳደቃቸውን የሚያወሳ ነው።ዋናው መሪው (ገጸ ባህርይ )ሀዲስ ሳህለሥላሴ ይባላል ።በዚያን ሰዓት ወይም በዚያን ጊዜ የነበረውን እንቅስቀሴ የነበረውን ድርጊትና ሁኔታዎችን በሃዲስ ያሳየናል ፣ያስቃኘናል ።ፊውዳላዊ አመለካከቶችን ፣አስተሳሰቦችን እንዲሁም ደግሞ ፊውደላዊ አገዛዝ ህዝቡን ምን ያክል እንደበዘበዘው ፣እንደዘረፈው ፣ የመደብ ስርዓቱ እንዴት እንደፈረሰ ወይም አፈራረሱን ያሳየናል ።ብዙ ሃያሲዎች መጸሐፉን ሃይሰውታል፣ አሞግሰውታልም በአብዮቱ ጊዜ (ወቅት) ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል በርቅዬው መጸሐፍ ብለውታልም።
ግዙት! ግዙት! ግዙት! አ.ን.ብ.ቡ.ት ።
#ሀዲስ..........................

ስልክ :-0992653968
0911704376

ግርባብ (ያ ደግ ሰው )ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለች ሽሙንሙን መጽሐፍ ጽፌ ሞቼ! የሚል ህልም ይሁን ራዕይ ነበረኝ።ደራሲ ና ሃያሲ  #አለማየሁ  #ገላጋይ ግርባብ (ያደግ ሰው ) :-ግርባብ አጠ...
23/07/2024

ግርባብ (ያ ደግ ሰው )
ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለች ሽሙንሙን መጽሐፍ ጽፌ ሞቼ! የሚል ህልም ይሁን ራዕይ ነበረኝ።
ደራሲ ና ሃያሲ #አለማየሁ #ገላጋይ
ግርባብ (ያደግ ሰው ) :-ግርባብ አጠር መጠን ያለች አብይ ወግ ሲሆን ተሽሞንሙና እና ተቀምማ የቀረበች መጸሐፍ ናት ።በተለይ በተለይ ረጅም ልቦለድ አፍቃሪዎች ይህች በተዋቡ ቃላትና በተዋበ አቀራረቡ የቀረበችውን ግርባብ ብታነቧት አሪፍ ነው እላለው ።ያ ደግ ሰው ዋና character ሲሆን እንዲሁም መንገደኛም ነው ።በየሄደበት በየተንቀሳቀሰበት ለሚያገኛቸው /ለሚያጋጥሙት ሰዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ይጠይቃል ስለ ህይወት ፣ስለ ሞት ፣ስለ ስራ ወ.ዘ.ተ የማይጠይቀው ጥያቄ የማያነሳው ሃሳብ የለም ማለት እንችላለን! ብቻ እያንዷንዷ ነገር ይጠይቃል :ጠይቆም አያቆምም :ይመልሳል። ህይወትን እዚው እንድናያት ፣እንድናሸታት የሚያደርግ መጸሐፍ ነው ።መጽሐፉን ግዙት መግዛትም ብቻ ሳይሆን አንብቡት ።
#ግርባብ(ያደግሰው)............................

ስልክ :-0911704376
0941845253

The 48 laws of power  (Robert greene)  ይህ መፅሐፍ እጅግ አደገኛና እጅግም አስፈላጊ መፅሐፍ ነው  ይላሉ! መፅሐፉን ያነበቡ ሐያሲያን መፀሐፉ በውስጡ 48 ህጎችን የያዘ...
22/07/2024

The 48 laws of power
(Robert greene)
ይህ መፅሐፍ እጅግ አደገኛና እጅግም አስፈላጊ መፅሐፍ ነው ይላሉ! መፅሐፉን ያነበቡ ሐያሲያን
መፀሐፉ በውስጡ 48 ህጎችን የያዘ ነው ።48 ህጎች ከታሪክ ከፍልስፍና እና ከተለያዩ መፅሐፍት እንደነ ና መፅሐፍቶች ተወጣጥቶ የተቀመመ ነው ።"
the 48 laws of power ለማህበራዊ ህይወት ለፖለቲካዊ ዓለም እና ለየትኛውም ግለሰብ አስፈላጊ ና የህይወቱ መመርያ ሊያደርገው የሚገባ ነው "
ይላሉ መፅሐፍቱን አንብበውና በመፅሐፍቱ ህይታችን ተለወጠ የሚሉ ሰዎች።ብዙዎ እንብበውታል ወደውታል።ብቻ ብቻ መፅሐፍቱን እንድታነብ Recommend አደርጋቸዋለሁ ። መፀሐፉ በአማርኛ ተተርጉሞ እና በ እንግሊዘኛ ይገኛል ።መጥተው ይጎብኙ
hawi book store
ስልክ :- 0911704376

Address

Abosto
Shashemene

Opening Hours

Monday 08:00 - 19:00
Tuesday 08:00 - 19:00
Wednesday 08:00 - 19:00
Thursday 08:00 - 19:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 19:00

Telephone

+251911704376

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when hawi book store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to hawi book store:

Share

Category