Øffîîň Bøňňă

Øffîîň Bøňňă Youtube

11/10/2022

"Gameessa,Namaa Hayyuu,Waan Dubbatu beekhu Maaliif akka Dubbatu,kabeekhu, Ustaz/Raayyaa Abbaamacca fii Ustaz Ibsaa/Qilleensi Nasrii Bubbise Page ,Umrii isaanii Rabbi Nuuf haadheereessu,🙏❗

09/10/2022
ረሱል (ሰ.ዓ.ወ) ይሰድብ የነበረ የዓይነ ስውሩ ለማኝ ታሪክበመዲና ከተማ መግቢያ በር ጥግ ላይ የሚለምን አንድ አይሁዳዊ ዓይነ ስውር ለማኝ ነበር። ይህ ለማኝ አላፊ አግዳሚውን ሲለምን ይውላ...
06/10/2022

ረሱል (ሰ.ዓ.ወ) ይሰድብ የነበረ የዓይነ ስውሩ ለማኝ ታሪክ

በመዲና ከተማ መግቢያ በር ጥግ ላይ የሚለምን አንድ አይሁዳዊ ዓይነ ስውር ለማኝ ነበር።

ይህ ለማኝ አላፊ አግዳሚውን ሲለምን ይውላል። እናም ወደ እርሱ ቀርበው ለሚመፀውቱት ሁሉ "ወንድሜ ሆይ
መሐመድን በፍጹም አትቅረብ እርሱ እብድ፣ ውሸታም እና ጠንቋይ ነው ። እርሱን ከቀረብክ በድግምቱ ትነካለህ እያለ የነቢዮ (ሰ.ዓ.ወ)ምን ስም ያጠለሽ ነበር

በአንፃሩ እርሳቸው ለዚህ ለማኝ ዘውትር ማለዳ ላይ ምግብ ይዘውለት ይመጡና ምንም መልስ ሳይሰጡት ይመለሳሉ

ለማኙ አይነ ስውር በመሆኑ ዘውትር ምግብ የሚያመጡለት ረሱል (ሰ.ዓ.ወ) መሆናቸውን እንኳ አያውቅም ነበር

አንድ ቀን ግን ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) ወደ አኪራ ሄዱ ወደ አኪራ ከሄዱ በኋላ ፣ነብዩ መሐመድ በቤተሰቦቻቸው፣በጓደኞቻቸው እና በአጠቃላይ በሙስሊሞች መካከል ጥልቅ ሀዘን ጥለው አልፈዋል።

ምክንያቱም ለአይነስውሩ አይሁዳዊ ለማኝ በየማለዳው ምግብ የሚያመጣለት አንዳችም ሰው አልነበረም።

በዚህ መሀል የህዝቡ አመራር በኡመር ኢብኑል ከጣብ እጅ ሆነ ። ኡመር የነቢዩን ውርስ ወጎች እና ፖሊሲዎች ለመከተል ወሰነ እና

ነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) በህይወት እያሉ ይከውኑት የነበረውን ተግባራት መከወን ጀመረ ከእለታት አንድ ቀን ኡመር የነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) ሴት ልጅ የሆነችውን የአሲያን ቤት ጎበኘ።
ከዚያም ልጄ ሆይ ከነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ) ተግባራት እኔ ያልሰራሁት አለ ወይ?” ሲል ጠየቃት

እርሷም እንዲህ አለች አባቴ ሆይ አንተ የሱና አዋቂ ነህ እና አባቴ ያደርገው ከነበው ተግባራት ያላደረግከው ነገር እንብዛም የለም ከአንድ ነገር በስቀር አለቻቸው

እርሳቸውም ምንድነው እሱ ብለው ጠየቋት ? አባቴ (ረሱሉላህ ) (ሶ.ዐ.ወ) በመዲና ከተማ መግቢያ በር ጥግ ላይ ቆሞ የሚለምን አንድ አይሁዳዊ ዓይነ ስውር ለማኝ ነበር። እርሱ ዘውትር “በየማለዳው ለዚህ ሰው ምግብ ይዘውለት ይሄዱ ነበር አለቻቸው

በማግስቱ ኡመር (ረዐ) ለዚህ ለማኝ ምግብ ሊሰጡት ወደዚያው አቀኑ፣ ለማኙ ዘንድ ደርሰው ያመጡትን ምግብ ለለማኙ መመገብ ጀመሩ ።

በዚህ ጊዜ ለማኙ በቁጣ አትመግበኝ ብለው አስቆሙት በንዴትም አንተ ማን ነህ ? ከአሁን በፊት ትመግበኝ የነበርከው ሰው አይደለህም ፣ ከአሁን በፊት ወደ እኔ ትመጣ የነበረው አንተ አይደለህም አለ ዓይነ ስውር ለማኝ "

ያሰው ወደ እኔ ሲመጣ እና ሲመግበኝ ለማኘክ አይከብደኝም ፣እሱ የሚያጎርሰኝ ለአፌ አስቸጋሪ አይደለም. ወደኔ ይመጣ የነበረው ሰው ሁል ጊዜ ይመግባኛል ነገር ግን መጀመሪያ ምግቡን ፈጭቶ ይሰጠኝ ነበር ብሎ ንግግሩን ቀጠለ ።

በዚህ ጊዜ ኡመር (ረዐ) እንባውን መቆጣጠር አቅቶት አለቀሰ፣ እያለቀሰ ለለማኙ እንዲህ አለው ዘውትር አወደ አንተ የምመጣ ሰው አይደለሁም።

እኔ ከጓደኞቹ አንዱ ነበርኩ፣ የተከበረው ሰው ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፣ እሱ የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ነው አለው ።

ለማኙም ይህን ሲሰማ ነቢዩን ይሰድባቸው ይዘልፋቸው ስለነበር ወዲያው ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ

ከዚያም የምትለኝ እውነትህን ነው አለው ? ለማኙ ቀጠለና እኔ ሁልጊዜ እሰድበው ነበር እርሱ ግን በፍጹም ምላሽ ሰጥቶኝ አያውቅም ፣ ይልቁንም በየማለዳው ምግብ ይዞ ወደ እኔ ይመጣ ነበር ፣ በጣም የተከበረ ሰው ነበር... አለ ዓይነ ስውሩ አይሁዳዊ ለማኝ ።

በመጨረሻ ሸሃዳውን በኡመር (ረዐ) ፊት አደረገ። በዚያን ጊዜ እና ከዚያ ቀን ጀምሮ ሙስሊም ሆኖ እስልምናን ተቀበለ

27/09/2022

Address

Jimma City
Muscat
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Øffîîň Bøňňă posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Øffîîň Bøňňă:

Shortcuts

Share