15/09/2024
የማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለትምህርት ስራ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ላስካ፡ ሐምሌ 19/2015 ዓ/ም (ላስካ ኮሙኒኬሽን)"ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ ቃል በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት እና በላስካ ከተማ አስተዳደር ት/ቤቶች ጽ/ቤት የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻልና የ2015 ዓ/ም የክረምት ወራት ተግባራት ዕቅድ ለማስፈፀም የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ መድረክ በላስካ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሄዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የላስካ ከተማ አስተደደር ዋና ከንቲባ ኢ/ር ዘማች ካንሶ ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት ነው ስባል የሁሉንም ሕብረተሰብ ተሳትፎ የሚፈልግ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ዋና ከንቲባው የትምህርት መሰረተ ልማት ካልተሟላ ትምህርት ወዳልተፈለገ መንገድ ስለምሄድ የሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ ያስፈልጋል ስሉ በአፅንዖት አሳስበዋል ፡፡
የማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለትምህርት ስራ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑንም ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ታምርሶ በበኩላቸው የትምህርት ጥራት ጉዳይ በጣም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል ትኩረት ልሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የትምህርት ስራን መንግስት ላይ ብቻ ጥለን የምንተው ጉዳይ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በእኔነት ስሜት ተነስተን በጋራ ተረባርበን ለዘርፉ ውጤታማነት ልንሰራ ይገባል ስሉ አሳስበዋል፡፡
ልጆቻችንን የነገ አገር ተረካቢዎችን ለማፍራት የትምህርት ቤቶችን ችግር በጋራ ልንፈታ ይገባል ስሉ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አወል ገዛኸኝ በርካታ ምሁራንን ያፈራው የላስካ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ67 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ቢሆንም በዕድሜው ልክ ያለማደጉን አስረድተው ከዚህ ትምህርት ቤት ተምረው ለወጡ ምሁራን በተማራቹበት ት/ቤት ላይ አሻራ እንዲታሳርፉ ስሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የተገኙት ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለዘርፉ ውጤታማነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ በመረሃግብሩ ከተገኙ ምሁራንና የማሕበረሰብ ክፍሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን የትምህርት መሰረተ ልማት ለማሟላት የሚያስችል የጋራ የውል ስምምነት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ሐምሌ 19/2015 ዓ/ም
#ላስካ