Tewahedo - ተዋህዶ እምነታችን

Call Directions

Tewahedo - ተዋህዶ እምነታችን The Ethiopian Orthodox Teahedo Church (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን)is the largest of the Oriental Orthodox Christian Churches

ወንድማችን አሌክሳንደር ፀጋዬ ይባላል :: ነዋሪነቱ አትላንታ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ሁለቱ ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው ዲያሊሲስ እያደረገ ይገኛል:: ህክምናውን ለመከታተል እና የኩላሊት እጥበቱን ...
12/29/2023

ወንድማችን አሌክሳንደር ፀጋዬ ይባላል :: ነዋሪነቱ አትላንታ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ሁለቱ ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው ዲያሊሲስ እያደረገ ይገኛል:: ህክምናውን ለመከታተል እና የኩላሊት እጥበቱን ለማድረግ የhealth insurance ስለሌለው ወጪው ከባድ በመሆኑና የሚረዳው የቅርብ ቤተሰብ ባለመኖሩ የእኛን እርዳታ ይፈልጋል:: ለወገን ደራሹ ወገን ነውና በቻልነው መጠን ለወንድማችን እንድረስለት::

“Blessed is the one who gives more than receives” - Acts 20:35 Dear extended family, friends,… Zebib Desta needs your support for Alexander Tsegaye Gonfa

01/10/2022

ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁ ነን!

“በህዝብ ገንዘብ ነው የተሰራው፣ ስለዚህ የሁሉም አደባባይ ነው የምትሉ ከሆነ ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁዎች ነን። መስቀል ማክበሪያ ቦታ እርስታችን ነው፣ የተዋህዶ ልጅ ደሞ ለእርስቱ ናቡቴን ነው!

ቀሲስ መምህር ዶክተር ዘበነ ለማ

01/08/2022
Share share share
02/26/2020

Share share share

  ?   ፡፡የቶ መስቀል በገጠራማው የሀገራችን ክፍል ልጃገረዶች ግንባራቸው ላይ በመነቀስ በግዜው ሀይማኖታቸውን ..ማንነታቸውን የሚገልፁበት መዋቢያቸው ነው(ለህቶቻችን ክብር አለኝ) አሁን ላ...
01/23/2020

?

፡፡
የቶ መስቀል በገጠራማው የሀገራችን ክፍል ልጃገረዶች ግንባራቸው ላይ በመነቀስ በግዜው ሀይማኖታቸውን ..ማንነታቸውን የሚገልፁበት መዋቢያቸው ነው(ለህቶቻችን ክብር አለኝ) አሁን ላይ በመቅረት ላይ ቢሆንም አሁን ላይ በደንብ የምናውቀው #በዴርቶጋዳ መጽሐፍ ላይ ይሁን እንጂ
#ሚስጥሩ በዛ ያለ ነው☞☞☞
ኢትዮጵያ የእየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል መገኛ የሆነች ሀገር ለክርስቶስ ያላቸውን ፍቅር ከልባቸው አልፎ በግንባራቸው ላይ በማጌጥ ለአለም ይመሰክራሉ።በአለም እንዲሁም በሀገራችን ብዙ አይነት የመስቀል አይነቶች ቢኖሩም የ ቶ መስቀል የምትጠቀም ፡፡
☞“ቶ” #የግዕዝ ሠባተኛዋ ፊደል ነች፡፡ ሠባት ቁጥር ትልቅ ትርጉም ያላት ነች #ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ሠባተኛው ዙፋን የጌታ እንደሆነ፣ ሠባተኛው ቀን ሠንበት እንደሆነች፣ 7 ቁጥር ብዙ ሚስጥር አላት፡፡
☞“ቶ” ሠባተኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ክርስቶስን የምትወክል ነች፡፡ ክርስቶስ ለኛ ሲል በቀራኒዮ መስቀል ላይ ራቁቱን መሠቀሉን የምታመለክት ነች። ትልቁ ከዚህ በላይ ያለው ሚስጥር ☞አባቶቻችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ትርጔሜ ሲተነትኑ በሰማይ መላዕክት ዘንድ ውጊያ ሆነ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ከሣጥናኤል ጋር ሲዋጉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈዋል፡፡
በሶስተኛው እንዲያሸንፉ ሲልካቸው ይህን ቀስተደመና ቀርፆ፣ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርፅ የ“ቶ” ቅርፅ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርፆላቸዋል። ለሁሉም "ኤል"የሚለውንም ሚስጢራዊ ስም አትሞባቸዋል።/አማኑኤል ከሚለው ከራሱ ስም መጠሪያ የተወሰደ ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ሀይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት ፅልመትን አልብሰው ወደ በርባኖስ ውስጥ ጥልቅ ጨለማ ላይ ወረወሩት።
የአምላክ ክንድ ፅኑ መሆኗን ሳጥናኤል ያውቃልና በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሴን ስሉስ ቅዱስ እያለ እየተንቀጠቀጠ ይገዛል ይላል። ሆኖም ምግባር ስለሌለው ፅድቅን አያያትም። ሰወች "ቶ"ን የህይወት ምልክት አድርገዉ የሚወስዱት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ነዉ::የሚገርመዉ ደግሞ ይህ ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብፃዉያን ቶርኔተር (የፑንት ምድር) ብለዉ በሚጠሯት ሀገር ነዉ::
ግብፃዉያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶርኔተር (የአሁኗ ኢትዮጵያ) ሰወችና አማልክቶች ነዉ:: በ670 አ.አ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረዉ ንጉስ ቲርሀቅ እየሩሳሌም የኦሶር ንጉስ በሆነዉ በሰናክሬም ስትወረር ለእየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ሀያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የ "ቶ" ምልክት እንደተቀረፀና ንጉሱም በ"ቶ" ቅርፅ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ፅሁፎች ተገኝተዋል:: .
የ"ቶ" ምልክት የተፈጠረዉ በቅርብ ግዜ ነዉ ለሚሉ ሰወች "ቶ "የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ ብል እዉነት እንጅ ዉሸት አይሆንም::ለዚህ ማስረጃየ ደግሞ የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ"ቶ" ቀመር መሆኑ ነዉ:: . ይህ ምልክት ግብፅ በሚገኙ የዋሻ ስእሎች ላይ የህይወትን ገፀ ባህሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ ምልክት አገልግሎት የጀመረዉ ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብፅ ላይ እንዴት ተገኘ? ብሎ ለሚጠይቅ ግብፅ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ንጉሶች ተጠቃሽ ናቸዉ::
ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል::ክራር ደግሞ
የኢትዮጵያ የባህል መሳሪያ መሆኑ አጀብ ያስብላል::
በሳባዉያን የዋሻ ላይ ስእሎችና ማህተሞች ላይ "ቶ" ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ (አስቻለዉ ከበደ የተባለ ፀሀፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ) በሚል መፅሀፉ አስፍሮታል:: ሳባዉያን ሰዉን ለመሳል "ቶ"ን መጠቀማቸዉ ይታወሳል፡፡ ወዳጆቼ ስለዚህ በግንባራቸው ላይ ቶ መስቀል የተነቀሱ እናቶቻችንን እህቶቻችንን ትልቅ አክብሮት ሊኖረን ይገባል እላለሁ።
እግዚአብሔር አምላክ ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
☞ #ላኮመልዛው

01/21/2020

ጥምቀት በ Washington DC

01/19/2020

Check Out Ethiopian News, New Ethiopian Musics, Ethiopian Comedy and Many More Ethiopian Videos by Subscribing. Unauthorized use, distribution and re upload ...

Address

Washington D.C., DC

Telephone

+12027798920

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewahedo - ተዋህዶ እምነታችን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category